Datasets:
text stringlengths 10 500 | audio audioduration (s) 10.1 60.5 | dialect stringclasses 1
value | speaker_id stringclasses 50
values | gender stringclasses 2
values |
|---|---|---|---|---|
ወጣቶችን አሳታፊ የሆነ ስራ ለመስራት በአካቢያችን/በቀበሌአችን ወጣቶችን አሳታፊ የሆነ ማህበር(ክበብ) በማቋቋም አካባቢያችን ተሰማርተው ይገኛሉ ለዚህ መልካም ስራቸው እንደ አርያ በመቁጠር የአካባቢዉ ሰዎች ለልጆቻቸው የወጣቶችን አርያ እንዲከተሉ የማስተማር እና የአካባቢው ሰው በሚሰባሰብበት ቦታ(አጋጣሚ) ላይ ደግ ስራ ለሰሩት የወጣቶን የሰሩትን በጎ ስራቸውን በመጥቀስ ምስጋና እና እውቅና ይሰጣል። | gojjam | XLJII7 | male | |
አዎን፣ እኔ በአንዳንድ ጊዜ ከጓደኞቼ፣ ከቤተሰቤ ወይም ከሌሎች ቅርብ ሰዎች ገንዘብ ልበድር እችላለሁ። በተለይ አስቸኳይ ጊዜዎች ላይ፣ እንደ አስቸኳይ መግዛት ያለብኝ ነገር ሲኖር፣ ከትምህርት ጋ የሚገናኝ ክፍያ ሱኖርብኝ ወይም ሌሎች አሳሳቢ ነገሮች ላይ ልበደር እችላለሁ። በዚህ ዓይነት ጊዜ ከቤተሰብ ወይም ከጓደኞቼ የማገኘው ድጋፍ በጣም ጠቃሚ ነው። ነገር ግን እነርሱ ራሳቸው የገንዘብ እጥረት ካላቸው በዚያ ጊዜ በተለይ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። | gojjam | XLJII7 | male | |
ወጣቶች በአካባቢ ጥበቃ የበለጠ መሳተፍ የሚችሉት መጀመሪያ በወጣቶች አእምሮ ውስጥ ስለ አካባቢ ጥበቃ አስፈላጊነት ግንዛቤ በመፍጠር ነው። ማለትም የነገ አገር ተረካቢ ዜጋ ስለሆኑ የአካባቢ ጥበቃ ላይ በንቃት ካልተሳተፊ መኖር እደማይችሉ የአየር ብክለት እንደሚያጋጥም :የደኖች መመናመን :የአፈር መሸርሸር :የወንዞች መቀነስ:የተሟላ ዝናብ አለማግኘት :የምርት እጥረት እንደሚያጋጥም በማስረዳት በስፋት እንዲሳተፉ ማድረግ ለዚህም ተነሳሽነት የሚያግዙ የትምህርት ቤት ክበቦችን በማጠናከር አስፈላጊውን ትኩረት በ... | gojjam | XLJII7 | male | |
የመስቀል :የገና :የጥምቀት :የትንሳኤ
በአላት ህብረተሰቡ እንደየ አቅሙ በተለያዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታዎች ይከበራል ። | gojjam | XLJII7 | male | |
በእኔ ቤተሰብ ውስጥ ልዩ ባህሪ አለው ብየ ማስበው ልጄ ነው.የ 8አመት ልጅ ነው,በጣም የተለየ የ ኳስ ፍቅር አለው.ጠዋት ማታም ምንም እረፍት የለውም ያገኘውን ነገር በእግሩ ሲመታ ነዉ የሚዉል.ኳስ ቢያጣ በ ሀይላንድ (በክዳኑ)ካልሆነም በአቩካዶ ፍሬ ይጫወታል ።ስለ ኳስ አንዲትም ዜና አታመልጠውም .የ ክለቦች ስም፣የተጨዋቾች ስም ሁሉንም ያውቃቸዋል።የ ሰፈር ልጆች CR7 ይሉታል የ ክርስቲያን ሮላንዶ አድናቂ ስለሆነ ። | gojjam | XLJII7 | male | |
በቀን ውስጥ ቢያንሰ አንድ ጊዜ እረፍት አደርጋለሁ። የእረፍት ጊዜዪ የማሳልፈው ቡና በማስፈላት፣ሻይ በመጠጣት፣ከጓደኞቼ ጋር በመዝናናት እና መዝናኛ ቦታ በመሄድ ቢያንስ ለአንድ ሰዓት ያህል የእረፍት ጊዜየን አሳልፋለሁ። | gojjam | XLJII7 | male | |
ወጣቶችን ከገጠር ወደ ከተሞች የሚያመጡ ትልቅ ሕልሞች ወይም ተጽዕኖዎች ከምናላቸው ከስራ ማጣት እና ከከተማ መስፋፋት (ቴክኖሎጅ፣የኢንዱስትሪ መስፋፋት )ጋር ተያይዞ የሚመጣ የፍላጎት ዕድገት ትልቁን ድርሻ ይይዛሉ።በተጨማሪም በከተማ የትምህርትእና የጤና አገልግሎት መስፋፋት እንዲሁም የሚፈልጉትን ህልም ለማሳካት በብዙ ነገሮች ከገጠር ይልቅ ከተማ የተሻለ ሆኖ በመገኘቱ።
የህይወት ለውጥ ወጣቶች እንዲያመጡ ከሚያነሳሷቸው ነገሮች አቻዎቻቸው ያሉበት ኢኮኖሚያዊ እና ስነልቦናዊ ዕድገት ላቅ ያለ መሆኑን በዋነኛነ... | gojjam | XLJII7 | male | |
አወ ሰዉ ከነበረዉ እዉቀት በተጨማሪ ሌላ የሙያ እዉቀት ሲወስድ አምሮዉ ይሰፋል የስራ ሞራሉም ይጨምራል።ምክንያቱም እረጅም ጊዜ የተማሩት ትምህርት ሊኖር ይችላል በዛ እዉቀታቸዉ ሳይጠቀሙበት ይሆናልነገር ግን "አጭርም ብትሆን ተስፋ የሚያስዝ ለስራ በአዲስ መልኩ የሚያነሳሳ" ሊሆን ይችላል በሌላም መልኩ "አጫጭር ስልጠና ወስደዉ ለስራ የበቁ ያዩ ይሆናል" እነዛም መልካም አርያ ይሆኗቸዋል።ደግሞም የበፊቱን እዉቀት መጠቀም ሲችሉ በአግባቡ ሳይጠቀሙበት ቀርተዉ ሊሆን ይችላል ስለዚህ፦< ያንን እድል በድጋሜ በት... | gojjam | XLJII7 | male | |
በወላጆች ስምምነት ብቻ ልጆችን ማጋባት | gojjam | XLJII7 | male | |
አዎን፣ የቁጠባ ልማዶቼ ከጊዜ በኋላ ተለውጠዋል። በተለይም እንደ ገንዘብ አስተዳደር፣ እና አስፈላጊ ነገሮችን ማስቀመጥ በግልጽ ሁኔታ ተሻሽሎል። ይህ ለውጥ ህይወቴን ያቀለልኝ ጥሩ ልምድ ነው እና የግል ግቤ ላይ ለመድረስ አርቄ እንዳስብ አደረጎኛል። ለዚህ ለውጥ ያነሳሳኝ ምክንያት ደግሞ ገንዘብ ባስፈለገኝ ሰዐት በቀላሉ ማግኘት አልቻልኩም ነበር ከዚ በተጨማሪ ደግሞ ቤተሰብ የሚሰጠኝን ምክር መተግበር በመጀመሬ ነው ። | gojjam | XLJII7 | male | |
ኢ.ቢ.ስ ቴለቪዥን ላይ የበስንቱ ተከታታይ ድራማ ሲሆን እያዝናና ቁምነገር ያስጨብጣል ። | gojjam | XLJII7 | male | |
በቤተሰብ ዉስጥ በዕለት ተዕለት ህይወት የቤት ውስጥ ኃላፊነቶችን መከፋፈል ጠቃሚ ነው። እነዚህ ኃላፊነቶች መከፍፈል ያለባቸው የቤተሰብ አባላት እንዳላቸው ጊዜ እና ችሎታ ነው ፤ ምክንያቱም ይህንን ያላገናዘበ ከሆነ የተሰጣቸውን ኃላፊነት ካለመወጣት ባሻገር ኃላፊነቱ በአንድ ወይም ሰው ላይ ብቻ ያረፈ ይሆናል። ቀደም ባሉት ጊዚያት በተለምዶ በቤት ዉስጥ ምግብ መስራት እና ልጆችን መንከባከብ የእናት ኃላፊነት፣ ቤት ማፅዳት እና እቃዎችን ማጠብ የሴት ልጅ ኃላፊነት፣ ትምህርት መማር የወንድ ልጅ እና ወጥቶ ሠር... | gojjam | XLJII7 | male | |
አንዳንድ የልጅነት ትዝታዎች የምንላቸው
1.ከትምህረት ቤት:
በትምህርት ቤት የተማርንው ፊደልና ቁጥር።
ትምህርት ቤት ከትምህርት ቤት የተምሳሌት ጨዋታ ወይም የወዳጅነት ጨዋታ።
2.ከሰፈር:
ከዳመና በታች በሰው ሰፈር መካከል የተሰየሙ የፈረስ ና የእንሰሳት ድምፆች።
3. የልጅነት ጨዋታ:
ማዘያ ጨዋታ አባባዬ አባባዬ ጨዋታ
ቀለም ሽቦ ጨዋታ ድንጋይ ከምር ጨዋታ::
4.ጓደኞች:
በአንድነት መዝናናት
ችግኝ መትከል
በበጎፍቃደኝነት ስራ ላይ መሳተፍ::
| gojjam | XLJII7 | male | |
በአንድ ርዕሰ ጉዳይ ላይ የተለያዩ አስተያየቶችን ስሰማ፣ የራሴን አመለካከት እማራምደው የግራ ቀኙን እሳቤ ከሰመው በኋላ፣ ክፋና ደጉን አዳምጨ ከሰመው እና ከተረደው በኋላ፤ የሚመስለኝን ሀሳብ በሚዛናዊ እና በፋትሀዊ መንገድ እሰነዝራለሁ። | gojjam | XLJII7 | male | |
የኛ ቤተሰብ በዓላትን እንደማንኛውም የ ካባቢው ማህበረሰብ ያከብራል። እንደ ሁኔታዉ ለበዓሉ የተዘጋጁ ነገሮችን ከጎረቤት ጋር በመቀማመስ እናሣልፋለን። ለምሣሌ ጠላ በመጠጣት፣ ደሮ ወጥ፣ ዳቦ፣ቡና በመጠጣት እንደሁኔታው እናሳልፋለን ማለት ነዉ። | gojjam | XLJII7 | male | |
የግል ህይወትና የስራ ሀላፊነት ከስራና ከመዝናኛ እንቅስቃሴዎች የየራሳቸው ሚና አላቸው።
የስራ እራሱን የቻለ ጊዜ እና ሰዓት አለው።
መዝናኛም ከስራ ሰዓት ውጭ የራሱን ጊዜ ሊጠቀም ይችላል እንጂ ከስራ ሰዓት ጋር አይገናኝም። | gojjam | XLJII7 | male | |
በአካባቢየ ያሉ ሰዎች ስለ አካባቢ ክስተቶች ከማህበራዊ ድረገጽ ፌስቡክ እና ቲክቶክ ይመርጣሉ ምክንያቱም ከመረጃ ተጨማሪ እንደ መዝናኛ ስለሚጠቀሙት:: | gojjam | XLJII7 | male | |
እሁድ ቤተክርስቲያን መልስ፣ወደ ቤተሰቦች በመሄድ መጠየቅ። | gojjam | XLJII7 | male | |
በሀገራችን የሚሰጡ የትምህርት ዘርፎች የሀገሪቱን ችግሮች ሊፈቱ በሚችል መልኩ እና በተሻለ ሙሁራን እንዲቀረጽ ማድረግ ቢቻል. ትምህርት ተቋማትን በማስፋፋት ሁሉም አካባቢ ተደራሽ ቢሆን እና ሙሁራንም ያላቸዉን ዕውቀት ሳይሰስቱ ቢያካፉሉ ,ለዚህም መንግስትም የሚገባቸውን ክፍያ ቢከፍላቸው እንዲሁም የተማረዉ ግለሰብ ደግሞ ከራሱ እድገት በዘለለ ሙያዉን የማህበረሰብ ችግሮችን በመፍታት እና የማህበረሰቡን እድገት በሚያረጋግጥ መልኩ ሊያዉለዉ ይገባል ። | gojjam | XLJII7 | male | |
እንደሚታወቀውበጎጃም ክፈለሀገር የባህላዊ ዘርፈብዙ ጭዎታዎች አሉ ከእነዚህም መካከል አንዱ የእስክታ ጭዎታ ወይም ባህላዊ ዘፈን ነው ይህም በደስታ ጊዜ የሚደረግ የደስታ መገለጫ ሲሆን ማህበረሰቡ እንደ ባህለ እና ወግ መሰረት ከቆዳ የተዘጋጅ የሙዚቃ መሳርያ ከበሮ በመያዝ የተቀመጠው የደስታ ተካፋይ እያጨበጨበ ከበሮው እየተመታ ጭፈራው ይቀጥላል።ከእነዚህ መካከል እንቅጥቅጥ፣ እስጉልድም፣አደግድግ፣የመሳሰሉትን ሁሉም በየተራ ይጨፍራል:: | gojjam | XLJII7 | male | |
አወ። የስራ ዕድል ፈጠራ። | gojjam | XLJII7 | male | |
ለምን ወደ እራሴ ማንነት አልመለስም እያልኩ እራሴን እወቅሳለሁ።ከጎደኛቸ ግብረ መልስ እጠይቃለሁ። | gojjam | XLJII7 | male | |
አደለሁም ግን ሰው በተለያየ መንገድ ሲሞት ስርዓተ ቀብሩን ለመፈፀምና ለመረዳዳት የተቋቋመ ድርጅት ነው። | gojjam | XLJII7 | male | |
''ገንዘብ ከሌለህ ማንም አይወድህም''ይለኘመ ነበር ጎደኛየ ጌታቸው ይህን ምክሩንና አባባሉን መቸም አረሳውም እውነቱንምዐነው እውቀት ኑኖኚ ይህ ስልክ ባይኖረኚ እናንተስ መቸ ታሰሩኚ ነበር እንደ ማለት ነው። | gojjam | UJUY1C | female | |
ያሉኝን በማድረግ እና ለነሱ በመታዘዝ። | gojjam | UJUY1C | female | |
"በእዉነት ፈጣሪ የአብርሃምን ትህትና አድሎሀል!! ፍፃሜህን ያሳምርልህ አመሰግናለሁ ለሌሎች አረአያ የምትሆን ሰዉ ነህ" ። | gojjam | UJUY1C | female | |
ሁለቱም ባል እናሚስት ሲጋቡ በፍቅር ወይም በእናት አባት ጥየቃ ይጋባሉ ።ሲጋቡ የቀለበት ስነስርዓት በተከናወነ
በሁለተኛ ቀን ዘመድ ትውውቅ ያደርጋሉ። | gojjam | UJUY1C | female | |
መረጃወችን ከቴሌቨዥን እናገኝለን ቀጥሎም ከቅየው ታሉ ሰዎች ለምሳሌ ቡና ለመጠጣት ሲቀመጡ ከሚያወጉት ወግ ከጡሩንባ ከሚለፍፉት እናገኛለን።
ከራድዮ እና ከቴሌቨዥን የምናዳምጣቸው ወጎችን አምናቸዋለሁ ምክንያቱም ስለተፈጠረው ወግ አጣርቶ ሰለሚያሳውቀን። እንዲሁም ስላለሁበት ቅየው ከመንደርተኞች በሚወጋ ወግ ለምሳሌ ከጥሩንባ ለፋፉወች፣ከድርተኞች ከሚመጣ ወግ አምናለሁ። የማምንበት ምክንያት መረጃው ከዛው ከቅርብ ሰለሚያገኙ። | gojjam | UJUY1C | female | |
እኛ የምንኖርበት ሠፈር የማህበረሰቡ የአኖኖር ዘይቤው አብሮ በመብላት፣አብሮ በመጠጣት እንዲሁም የተቸገሩትን በመርዳት ይታወቃል።ሌላው ደግሞ ከብረባእላትን ለምሳሌ አዲስአመት፣ገና፣ጥምቀት፣፣ፋሲካ፣አረፋ፣መውሊድ የመሳሰሉትን ባህሎች እንደየሀይማኖቱ የቱፊት ሥርአት በጋራ ና በድምቀት እንዲሁም የሚያስፈልጉ የባህል አልባሳትን በመልበስ በድምቀት ሲያከብር ይኖራል።ሌላው የአካባቢያችን የማህበረሰቡ መገለጫ የሆነው አንድ ሰው ቤተሰቡን በሞት ሲለየው የአላቅሱኝ መልእክት በጥሩንባ ይተላለፋል ከዚያ በኋላ በሀዘን የተጎ... | gojjam | UJUY1C | female | |
በአካቢያችን የተለያዩ የእድር አባላት በቡድን በቡድን እየሆኑ በሳምንት አንዴ ከቤተክርስቲያን መልስ ተሰባስበው በመወያየት እና ቋሚ የገንዘብ መዋጮ በማዋጣት በመተዳደሪያ ደምባቸው መሰረት ከቤተሰብ አባላት ውስጥ ድንገተኛ ሞት ሲከሰት ከተጠራቀመ መጠባበቂያ ገንዘብ በማንሳት የተለያየ ምግብ እና መጠጦች በማዘጋጀት (በማቅረብ) ለሀዘን የተቀመጠውን ሰው በመጋበዝ የሚሸኙበት እና በሀዘን ለተጎዳው ሰው የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግበት ጥሩ እና ጠቃሚ የቆየ ልምድ ነው። | gojjam | UJUY1C | female | |
ከባድ ነው ምክንያቱም ውሳኔ ከወሰነ በኋላ ውስጣችን ትክክል እንዳልሆነ ሲገባን እና ትክክለኛውን ነገር ስናውቅ በእጃችን የነበረውን ነገር ልናጣው ስለምንችል እናም እራሳችንን ወደ መውቀስ እና የአዕምሮ እክል ሊገጥመን ይችላል።
ደስታንና ሰላም ይፈጥራሉ እናም ደግሞ ትዳርን ፣ ጓደኝነትን ፣ አብሮ ሠራተኝነትን ከመፍረስ ይታደጉታል | gojjam | UJUY1C | female | |
ፊልም ማየት ኳስ ማየት እራሴን ለማዝናናት በጣም ደስተኛ ያረገኛል | gojjam | UJUY1C | female | |
የ3ኛ አመት የዩኒቭርሲቲ ተማሪ በነበረሁበት ስዓት የአንድ ኮርስ መምህራችን ኮርሱን ከሚያስተምረው በላይ አመለካከታችን ለመቀየር የሚፈጀው ጊዜ ይበልጥ ነበረ። በወቅቱም ነበር በከፊልም ቢሆን የተረደሁት። | gojjam | UJUY1C | female | |
በአካባቢያችን የመሠረተ ልማቶች እምብዛም ባይሆኑም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከተከናወኑ ልማቶች ውስጥ የኮርዲር ልማት ተጠቃሹ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ የአየር መንገድ እድሳት ሌላኛው ነው:: ይህም አካባቢያችን ፅዱና ለመኖር አመቺ እንዲሆን አድርጎታል ። ነገር ግን ከተማችን የቱሪስት መዳረሻ እንደመሆኗ መጠን ዋና ዋና የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች ላይ ለምሳሌ የጣና ሀይቅና አባይ ተፋሰስ አካባቢዎች ዙሪያ አሁንም ሰፊ ስራን ይጠይቃል። | gojjam | UJUY1C | female | |
የመጀመሪያው የእጅ ስልካችን ነው ። ከፍ ሲል ደግሞ ማህበራዊ ሚዲያዎች ለምሳሌ (ኢሞ ዋትስአፕ ቴሌግራም እና ቲክቶክ ) እና ሌሎችም የዘመኑን ትውልድ የዋጀ ቴክኖሎጂ 4 ጂ 5ተኛውን ትውልድ በመጠቀም በድምፅእና በምስል በታገዘ መልኩ ይገናኛሉ።መስተጋብሩ እጅግ ከፍ ብሏል | gojjam | UJUY1C | female | |
ለሰራ አጦች የስራ እድል እፍጥራለው ለምሳሌ የስራ እጥ ቆጥሮችን ለመቀነስ | gojjam | UJUY1C | female | |
የወንድ ልጅ ግርዛት ምክንያቱም በአሁኑ ሰዐት ብዙ ወጣቶች በልጅነታቸው አይገረዙም ትልቅ ከሆኑ በኋላ በዘመናዊ መንገድ እንገረዛለን በማለት። | gojjam | UJUY1C | female | |
በብዙ የኢትዮጵያ ማህበረሰቦች፣ ወንድና ሴት ለመጋባት ሲወስኑ የመጀመሪያ እርምጃው በቤተሰቡ መካከል መደበኛ የሆነ መግቢያን ያካትታል። ከሙሽራው ወገን ሽማግሌዎች ወይም የተከበሩ ተወካዮች (ብዙውን ጊዜ "ሺማጊል" ይባላሉ) የሙሽራዋን ቤተሰብ መጎብኘት እጇን ለጋብቻ ይጠይቃሉ። ይህ ሂደት፣ “ሽማግሌ መላክ” በመባል የሚታወቀው፣ ድርድርን፣ ስለ ጥሎሽ ውይይቶችን እና በረከቶችን ያካትታል። ይህ የመከባበር ምልክት እና በቤተሰብ መካከል መተማመንን ለመፍጠር መንገድ ነው. ይህ ባህል ጋብቻው ከመፈጸሙ በፊ... | gojjam | UJUY1C | female | |
በልጅነቴ ትምህርት ቤት ከማስገባት ይልቅ ቤተሰብ መዳር ይፈልጉ ነበር ምክንያቱም በማህበረሰቡ ዘንድ ልጅን መዳር እንደ ትልቅ ነገር ስለሚቆጥሩት ነው ።እኔ ግን ላጋጠመኝ ችግር እጅ ባለመስጠት ቤተሰብን በማሳመን ማለትም አሁን ባገባ በችግር ላይ እደምወድቅ ህይወቴም እደሚበላሽ ይህም እናንተን ያስደስታችሇል ብየ አላስብም ተምሬ ነገ ትልቅ ደረጃ ከደረስሁ በሇላ የፈለግሁትን ማግባት አና እናንተንም መርዳት እችላለሁ ብየ ወላጆቸን በማሳመን ያን ችግር ተቋቁሜ ዛሬ ካሰብሁት ደረጃ ላይ ደርሽ አገኛለሁ ። | gojjam | UJUY1C | female | |
በአካባቢዬ የቅርብ ጊዜ የተከናወነው የመሠረተ ልማት ፕሮጀክት መካከል ከፍተኛ ተጽእኖ ያሳየው የአዲሱ አውራ ጎዳና በክፍለ ሀገር ነው። በፍጥነት መጓጓዣን አስቸጋሪ ያደረገው ብዙ ችግኝ ቀርፎ ብዙ ጊዜን መቆጠብ ጀመረ።
ነገር ግን አሁንም ሊሻሻል የሚያስፈልገው ብዙ ነገር አለ። በተለይ የቆሻሻ አወጋገድ እንዲሁም በአውራ ጎዳናው ላይ የድህነት ቅርብ እንክብካቤ ይፈልጋል። ተጨማሪ የመንገድ መብራት፣ ትራፊክ ምልክቶች እና ዕፅዋት ማሻሻያም በጣም ያስፈልጋል።
| gojjam | 0G2FAS | female | |
በአካባቢያችን ያሉ በእድሜ የገፋ ሰዎች ከወጣቶች በተለየ መንገድ ስሜታቸውን የሚያሳዩት፣ ከወጣቶች ጥሩ የሆነ ስነ-ምግባር ስለማይመለከቱ ነው። በእድሜ የገፋ ሰዎች ለአገር እድገት እና ክብር ተቋርቋሪ፣ ከእነሱ በእድሜ ከፍ የሚሉትን አክባሪ፣ በጀግንነታቸ ውም የአገርን ዳርድንበር በወኔ በቁርጠኝነት የማያስደፍሩ በመሆናቸው፤ ወጣቱም የእነሱን አርያ የማይከተል ልፍስፍስ፣ እራስ ወዳድ፣ የአገሩን ታሪክ የማያውቅ፣ ታላላቆችን የማያከብር፣ በአቋራጭ መክበር የሚፈልግ፣ በሱስ የተለከፈ፣ በመሆኑ በዚህ ምክንያት ... | gojjam | 0G2FAS | female | |
ተማሪዎች በትምህርታቸው ስኬታማ እንዲሆኑ የሚያነሳሳቸው በተለያዩ ምክንያቶች ናቸው ። ለምሳሌ:- ከመምህራን እና ከወላጆች ማበረታቻ፣ ሙገሳወች ፣የተለያዩ ሸልማቶች ሲያገኙ እና አወንታዊ የመማሪያ አካባቢ፣ እንደ መጽሐፍት እና ቴክኖሎጂ ያሉ ግብዓቶችን ማግኘት ሲችሉ እና አጋዥ ቡድኖች እንዲኖሩ በማድረግ ወሳኝ ሚና ይጫወታል ። ለርዕሰ ጉዳዮች ግላዊ ፍላጎት፣ ውጤታማ ጊዜ አያያዝ እና ራስን መግዛት የበለጠ ሊያበረታታቸው ይችላል። ከዚህም በላይ ትምህርትን ከወደፊት እድሎች ጋር ማገናኘት እንደ ሙያ ... | gojjam | 0G2FAS | female | |
የተሳሳተ መረጃ ወይም አግባብነት የለለው መረጃ በጣም ለተለያዩ ችግሮች ያጋልጣል።ለምሳሌ እኔ ፈተና አልፎኝ ያውቃል፦አንደኛ አመት እያለን ስልክ አልነበረኝም እና እና አንድ አስተማሪ ፈተና 10 ሰአት ይኖራል ብሎ በቴሌግራም ተናግሯል።ከዚያ ጓደኛየን ምን ተባለ ሰለፈተና ስለው 10 አለኝ ለካስ አስተማሪው በሀገሬኛ ሰአት አቆጣጠር ሳይሆን በእኛ 4 ሰአት ጠዋት ነው ብሎ የነሮ። ያው እኔ 10 ሰአት ስሄድ ፈተና የለም ብጠብቅ የለም። ከዚያ አንድ ተማሪ ሳገኝ እንዴ ምን ነካህ ፈተና እኮ ጠዋት ነበር አለኝ ።... | gojjam | 0G2FAS | female | |
በጥዋት ተነስቸ ከምከውናቸው የቤት ዉስጥ ተግባራት መካከል፦ በመደመሪያ ለልጆቸ ቁርስ መስራት፣ ምግባቸውን መቋጠር፣ ልብሳቸውን በማልበስ ልጆችን ወደ ትምህርት ቤት መሸኘት ነው። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በጧት ተነስቸ የማከናውናቸው ተግባራት ቢኖር ለቤተሰቡ አባላት ቁርስ መስራት፣ ቤት መወልወል፣ አልጋ ማንጠፋ፣ ቤትን ማስተካከል፣ ውሀ መቅዳት፣ የጨቅላዋን ልብስ ማጠብ፣ የጨቅላዋን ወተት ከሰፈር ማምጣት ነው፣ እንዲሁም የጓሮ አታክልቶችን መኮትኮትና ውሀ ማጠጣት ነው። | gojjam | 0G2FAS | female | |
አዎ ዛሬ ለሰዎች ብዙ ጠቃሚ ትምህርቶችን የሚያቀርቡ ልዩ ታሪኮች ዘፈኖች እና ጥበባዊ አባባሎች አሉ። ከእነዚህም መካከል በተለይም በሰዎች ህይወት ላይ ለማስታዎቂያና ለማሳሰቢያ የሚያገለግሉ ናቸው።
ከእነዚህም ከሚሰጡት ትምህርቶች አንዳንዶቹ የሚከተሉት ናቸው፦
1.የአለፋው የታሪክ ትምህርት
2.በዘፈኖች ውስጥ የምሳሌና የማስተማር ሒደት
3.በጥበባዊ አባባሎች መካከል የፍቅር የሰብአዊነትና የአንድነት ተምሳሌት ሒደት
በአጠቃላይ ልዩ ታሪኮች ዘፈኖች እና ጥበባዊ አባባሎች በከፍተኛ ትምህርት የሚያቀርቡ ናቸ... | gojjam | 0G2FAS | female | |
በመጀመሪያ ትህምርት ማለት የባህሪ ለዉጥ በመሆኑ በህይወቴ ላይ መዘጋጀትን አምጥቶልኛል።
ይህም እንዴት ነው ቢባል በመማሬ ነገሮችን እንድንመረምር እና እንዳስተውላቸው አድርጎኛል ። በተማርኩት ዘርፍ ደግሞ እንደ ሂሳብ ተማሪነቴ ትህምርትን መማሬ በገንዘብ አየየዝ፣ በገንዘብ አጠቃቀም እና አመጣጥ ላይ ትልቅ የሆነ እዉቀትን አግኝቼበታለሁ።ከዛም በተረፈ ሌሎችን ቤተሰቦቼን እና ጓደኞቼን ስለ ገንዘብ አያያዝ፣ አጠቃቀም እና አመጣጥ በአቅሜ ልክ አሳዉቃቸዋለሁ። | gojjam | 0G2FAS | female | |
የአካባቢው የውሃ ሁኔታ ካለፉት አመታት ጋር ሲነጻጸር የበለጠ ፈታኝ እና ከባድ ሆኗል። በአየር ንብረት ለውጥ፣ በሕዝብ ቁጥር መጨመር እና በመጥፎ የሀብት አያያዝ ምክንያት የውሃ አቅርቦት ቀንሷል። በአንዳንድ አካባቢዎች ድርቅ እና የውሃ እጥረት በብዛት አለ ። የውሃ ጥበቃን ለማሻሻል የተለያዩየ ነገሮች አሉ እነሱም የዝናብ ውሃ ማጠራቀም ፣ የውሃ ፍሳሽ ማስተካከል፣ የውሃ ቆጣቢ መሳሪያዎችን መጠቀም እና የህብረተሰቡን ግንዛቤ የማሳደግ መፍትሄዎች አሉ ። የህብረተሰቡ ተሳትፎ እና የመንግስት ድጋ... | gojjam | 0G2FAS | female | |
የሌላ ሰው ቤት በእንግድነት በምንሄድበት ወቅት፣ ለተቀባዮ እና ለቤተሰባቸው ያለን አድናቆት እና አክብሮት እጅግ ላቅ ያለ ነው። በመጀመሪያ የእግዜሄር እንግዳ ነኝ በማለት እጅ ይነሳ፣ ሰላምታም እንለዋወጣለን፣ ስለ ሀገሩ፥ ስለ ቀየው፥ ሰለ መንደሩ ደህንነት፥ ስለ ልጆች ጤንነት፥ ስለ ከብቶች፥ ስለ አዝመራው ባጠቃላይ ስለ ሁሉም ነገር ከሞላ ጎደል ይወሳል፥ ይጠየቃል፥ ይወራል። ስለ አደረጉት መስተንግዶ እንግዳ አቀባበል፤ አድናቆት እና አክብሮት ምርቃትና ምስጋና፣ ውዳሴ፣ ዘፈን፣ በግጥም ወዘተ ይቸራቸዋል ... | gojjam | 0G2FAS | female | |
በአካባያችን ያሉ በእድሜ የገፉ ሰዎች ወጣቶች ወይም ልጆች ከባህላቸው ያፈነገጠ አለባበስ ወይም ወጣ ያሉ ንግሮች ሲያስተውሉ የመገሰፅ እና ለሌሎች ልጆች ስማቸውን በመጥቀስ ''እንደ አያ እገሌ ልጅ '' እንዳትሆኑ በማለት እንደማስተማሪያነት ይጠቀሙባቸዋል።በእድሜ የገፉ ሰዎች ሬዲዮ እና ቴሌቪዠን ዋና መረጃ ማግኛቸው ሲሆን ወጣቶች ለቴክኖሎጂ ቅርብ ስለሆኑ የተለያዩ ሚዲያዎችን ይጠቀማሉ ይህ ልዩነት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እንዴት እንደምንወያይ ያሳያል። ወጣቶች የተለያዩ ዘመናዊ ነገሮችን ያመጣሉ፣ ሽማግሌዎ... | gojjam | 0G2FAS | female | |
እራሴን አና ቤተሰቤን የምደግፈው ብዙውን ጊዜ የመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ በኮንትራት ተቀጥሬ በየወሩ ከማገኘው ደሞወዝ ነው።አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የመንግስት ኮንትራት ሥራ ሲቋረጥ እና ሲጠፋ ለተወሰነ ትንሽ ጊዜ ለአማካሪ የግል ድርጅቶች ጥሬ መረጃዎችን በመሰብሰብ በቀን አበል በሚከፍሉኝ ገቢ ከምግብ እና አልጋ ወጭ የተረፈችውን ለቤተሰቦቼ እልካለሁ።በዚሁ በተቆራረጠ የገቢ ማስገኛ ስራ መንገድ አብረው የሚኖሩትን ልጆቼን አና ባለቤቴን እያስተዳደርኩ እገኛለሁ። | gojjam | 0G2FAS | female | |
ጤንነትን እና ደህንነትን ለመጠበቅ የሚረዱት አስፈላጊ ነገሮች እነዚህን ነገሮች አደርጋለሁ።
⦁ ጤናማ አመጋገብ፣ በቂ ውሃ መጠጥ፣ አትክልትና ፍራፍሬ መብላት
⦁ መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ (ማለትም መራመድ፣ ዮጋ ወይም ሌሎች እንቅስቃሴዎች)
⦁ ጭንቀትን መቆጣጠር እና የአእምሮ ጤናን መከታተል
⦁ በተደጋጋሚ እጆችን መታጠብ እና የንጽህና ልምዶችን መከተል
⦁ ስጋራን እና አልኮልን መቆም
⦁ በቤተሰብ እና ጓደኞች ደጋፊ መሆን እና ስሜታዊ ድጋፍ መፈለግ እና በየ ሳምንቱ ወይም ወሩ አስፈላጊ ነገሮች ችክ... | gojjam | 0G2FAS | female | |
እኔ በምኖርበት አካባቢ፦ ትምህርት ቤትችም ፣ክሊኒኮችም እና ቀበሌ ጽ/ቤቶች አሉ።ያው ትምህርት ቤቶች ከኬጅ እስከ ዩንቨርስቲ ድረስ አገልግሎት ለማህበረሰቡ ይሰጣሉ። ከግል እስከ መንግስት ትምህርት ቤቶች አገልግሎት በእውቀት እና በስነ-ምግባ የታነፀ ትውልድ መገንባት ላይ ናቸው።ክሊኒኮች በየ ሰፈሩ አገልግሎት ይሰጣሉ። ከኒኖችን መርፊወችን ከሀኪም የሚመጡ ትዛዞችን ለማህበረሰቡ አገልግሎት ይሰጣሉ።ቀበሌ ፅ/ቤቶችም የተለያዩ አግልግሎቶችን ለምሳሌ ፦የኗሪነት መታወቂያ መስጠት፣የልደት እናወሳኝ ኩነት አግልግሎ... | gojjam | 0G2FAS | female | |
አካባቢያዊ የጤና ስርዓታችንን አንድ ነገር መቀየር ብችል በቀጥታ የጤና አገልግሎት በገጠር አካባቢ መዳረስን ነበር የምንለውጠው ። ብዙ ጊዜ ህክምና ቤቶች በቂ መድሀኒት የላቸውም፣ ባለሙያ በቁጥር እጥረት አለ፣ ታካሚዎችም ሩቅ ከተማ እንዲመጡ ይገደዳሉ። ነገር ግን በአካባቢያችን የሚታወቀው ጥሩ ነገር የህፃናት ጤና በግልጽ ትኩረት መሠጠቱ ነው፣ በእርግዝና ወቅት ክትባትና እንክብካቤ በጥሩ ሁኔታ ይሰጣል። እንዲሁም የመከላከያ ክትባት ልጆችን ከብዙ በሽታዎች እየጠበቀ ነው። | gojjam | 0G2FAS | female | |
1. የመኖሪያ መረጃ ማግኘት (የመኖሪያ ማረጋገጫ፣ ቤት ቁጥር ወዘተ)
ቤተሰብ መዝገብ ወይም የመኖሪያ ማረጋገጫ ለመያዝ፣
በሌላ ቦታ የተከራዩ ነዋሪዎች አዲስ መኖሪያ ለመመዝገብ፣
የነዋሪ መረጃ ለመያዝ (ምሳሌ፡ በሰነዶች ላይ የሚፈለግ መረጃ)።
2. አስተዳደራዊ እና ህጋዊ አገልግሎቶች ለማግኘት
የአመራር ጉባኤ ምክር ወይም የተመረጡ ተወካዮች ጋር ለመወያየት፣
የተቆጣጠሩ ጉዳዮችን (በማኅበረሰብ ውስጥ በተከሰተ ግጭት ወይም ችግር) ለማቅረብ፣
ማንኛውም ቅሬታ ወይም መግለጫ ለማቅረብ።
3. ማህበራዊ ድጋፍን ለመ... | gojjam | 0G2FAS | female | |
ይበልጥ ማራኪ ሆኖ ለመኖር በወጣቱ ዘንድ ሊለመድ የሚገባ ነገር ቢኖር የጋራ ድጋፍ ስርዓቶች ናቸው። ምክንያቱም ሰው በባህሪው ሙሉ እና ሁሉን አዋቂ ስላልሆነ መደጋገፉ አንዱ የሌላውን ጉድለት እንዲሞላ ያስችላል። ሊለመድ የሚችለው ደግሞ በማህበራዊ መስተጋብሮች ውስጥ በንቃት በመሳተፍ ነው።ስለዚህ የጋራ ድጋፍ ስርአቶች በጣም አስፈላጊ እና እንደባህልም ሊለመድ ሊጎለበት የሚገባው የጋራ እሴት መሆን አለበት። | gojjam | 0G2FAS | female | |
በአለም ውስጥ በየትኛውም ቦታ መጓዝ ከቻልኩ ጃፓንን እመርጣለሁ. በዓይነቱ ልዩ በሆነው የጥንታዊ ወጎች እና የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ውህደቱ ይማርከኛል። ውብ ቤተመቅደሶችን፣ ባህላዊ የሻይ ሥርዓቶችን እና የቼሪ አበቦችን ለማየት ወደ ኪዮቶን መጎብኘት እፈልጋለሁ። የቶኪዮ ደማቅ የከተማ ህይወትን፣ የላቁ ፈጠራዎችን እና እንደ ሱሺ እና ራመን ያሉ ልዩ ምግቦችን ማሰስ አስደሳች ይሆናል። ራሴን በባህሉ ውስጥ መዝለቅ፣ ታሪኩን ማወቅ እና የተፈጥሮ ውበቱን እንደ ፉጂ ተራራ እና ፍልውሃዎች በመደሰት ጉዞውን አስተ... | gojjam | 0G2FAS | female | |
የሚያሳዩት የባሕሪ ለዉጥ፦ዝምተኛ የነበሩ ልጆች ተጫዋች እና አኩራፊ ልጆች ሳቂታ ይሆናሉ ናፋቂና አልቃሻ ይሆናሉ።የአመጋገብ ስርዓታቸው ይስተካከል ፣የአለባበስ እና የንጽሕና አጠባበቅ ሁኔታወችን ለይተዉ ያቃሉ፣ ለጫወታ ያላቸዉን ጊዜ ይቀንሳሉ ምክንያቱም ትኩረታቸዉ ወደ ትምሕርታቸዉ ስለሚሆን፣ጊዜያቸዉን በአሉባልታ ነገር አባካኝ አይሆኑም ፣ብዙ ጓደኞችን የፈራሉ፣ከሰወች ጋር ያላቸውን ግንኙነት ይጨምራል፣ሰወችን አክባሪ ይሆናሉ ፣ታዛዥና ትሁት ይሆናሉ። | gojjam | 0G2FAS | female | |
ስለ እርግዝና ወይም ወሊድ ስናስብ ከዚህ ቀደም ቡዙ እናቶችን እና ጨቅላ ህፃናቶችን በሞት እንዳጣን እናስታውሳለን።ሆኖም ግን በአሁኑ ሰአት ስለእርግዝና ወይም ከወሊድ በኋላ ስለሚደርግ ባህላዊ እንክብካቤ እንዲሁም በየጤና ተቋማቱ የሚሰጡ ቅድመ ወሊድ እና ድህረ ወሊድ እየተባሉ የሚደረጉ የህክምና ክትትሎች አሉ።አንድ እናት ከወለደች በኋላም በጤና ተቋም ለተወሰነ ቀናት በመተኛት አስፈላጊውን ክትተል ይደረግላታል።እነዚህ ነገሮች በትኩረት መቀጠል አለባቸው።መቅረት ያለባቸው ጎጂ ልማዳዊ ነገሮች ቤት ውጥ መወ... | gojjam | 0G2FAS | female | |
በአካባቢያችን የሚዘወተሩ የእጅ እና የእንጨት ስራዎች ናቸው። የእጅ ስራዎች የምንላቸው የኪሮሽ ስራ፣ጥልፍና ስፌት በዋነኛነት ተጠቃሽ ሲሆኑ የእንጨት ስራ ደግሞ የተለያዩ ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ እንዲሁም ዘመናዊ የቤት እና የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶች ይገኛሉ። ለምሳሌ ያህልም መስቀል፣ከበሮ፣ወንበር፣ጠረጴዛ እና ሌሎች ታሪካዊ አንድምታ ያላቸው ቅርፃ ቅርፆች በብዛት ይሰራሉ። እነዚህ ቅርፃ ቅርፆች በቤት እና በቢሮ ውስጥ እንደ መገልገያ እና ማስዋቢያነት እንጠቀምባቸዋለን። አንዳንዶችን ደግሞ ሃይማኖታዊ ሲሆኑ ... | gojjam | 0G2FAS | female | |
የእድር አባል መሆን በርካታ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ስነ-ልቦናዊ ጥቅሞች አሉት። ከዋነኞቹ ጥቅሞች መካከል ጥቂቶቹ ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፦
1. ማህበራዊ ትስስር እና የጋራ መረዳዳት
* ሀዘን መጋራት: እድር በዋነኛነት ለቅሶ ላይ ተገኝቶ ቤተሰብን ማጽናናት እና ስርዓተ ቀብርን በጋራ ማከናወን ትልቅ ሚና ይጫወታል። አባል የሆኑት ሰዎች የሀዘን ጊዜያቸውን ብቻቸውን እንዳያሳልፉ ይረዳቸዋል።
* ደስታን ማካፈል: እድር በሀዘን ጊዜ ብቻ ሳይሆን በደስታ ጊዜም ይረዳዳል። ለምሳሌ፣ የሠርግ ወይም የጥምቀት... | gojjam | 0G2FAS | female | |
በአካባቢዬ ካለው ሁኔታ አንፃር ብችል ልለውጠው የምፈልገው የፈሳሽ ቆሻሻና የደረቅ ቆሻሻ በደምብ በተለያየ መንገድ እንዲወገድ ማድረግ ነው። የውሃ መፋሰሻ ቦዮች በደንብ የተስተካሉና በየጊው ጥገና የሚደረግላቸው እንዲሆኑ አደረግ ነበር። እነዚህ በጤና ሁኔታ ላች ችግር ስለሚፈጥር።
በወባ በሽታ ላይ ሲሰራ የነበረው ጥሩ የሚባል ነበር። የኤች አይ ቪ ስርጭትን ለመከላከል ሲሰራ የነበረው ጥሩ ነበር። አሁን አሁን በተለይ በኤች አይ ቪ ስርጭትን ለመከላከል ላይ ያለው ስራ ካም ሆኖል። | gojjam | 0G2FAS | female | |
ለአካባቢየዬ ጥሩ፣ እውነተኛ፣ ፈጣን፣ ሳቢ፣ ታማኝነቱ የተረጋገጠ፣ ዜና ለማድረስ የሚያጠቃልላቸው ነገሮች፣ ቋንቋ፣ የድምፅ መልዕክቶች፣ ጽሑፎች፣ ይሆናሉ።
የሚካተቱ ርዕሶችም፣ ስለ መስቀል ደመራ በዓል አከባበር፣ አሁን ትምህርት የሚከፈትበት ወር በመሆኑ የተማሪዎች ምዝገባ እና አጀማመር፣ አሁን ወቅቱ ክረምት ስለሆነ ስላለው የዝናብ ሁኔታ፣ አሳሳቢ እና አንገብጋቢ ስለሆነው የሠላም ጉዳይ፣...ወ.ዘ.ተ. ይሆናሉ።
አሁንጊዜው የቴክኖሎጅ ዘመን ስለሆነ ዜናዎችን ወደ ማህበረሰቡ ሊደርሱባቸው የሚችሉ የዜና... | gojjam | 0G2FAS | female | |
መጀመሪያ ላይ ጊዜ ያለፈበት መስሎኝ የነበረው ግን በኋላ ላይ ጠቃሚነቱ የገባኝ ትልቅ ሰው የሰጠኝ የጤና ምክር “ምግብህን በደንብ አኝከህ ብላ” የሚለው ነው።
መጀመሪያ ላይ የነበረኝ ግንዛቤ
ይህን ምክር ስሰማ ወዲያውኑ ወደ አእምሮዬ የመጣው ትምህርት ቤት ሳለሁ መምህራኖቻችን “ምግብ በደንብ ማኘክ ለምግብ መፈጨት ሂደት ጥሩ ነው” ብለው ያስተማሩኝ ነገር ነው። ምክሩ ከጊዜው የዘመኑ የጤና መረጃዎች ጋር ተያያዥነት የሌለው የድሮ ሰዎችን ልማድ ይመስል ነበር። በዚያን ጊዜ፣ ጤናን በካሎሪ፣ በፕሮቲን እና በካ... | gojjam | 0G2FAS | female | |
በሕይወቴ ዉስጥ አስፈላጊ ዉሳኔዎችን በአብዛኛው የምወስነው በአካል ወይም በስልክ ደውየ ከማገኛቸው ጓደኞቼ ጋር በመወያየት ነው።ይህ በእራሴ መወሰን ያለ መቻል ልምድ በህይወቴ ላይ አንዳንድ ውሳኔዎች ዛሬም ድረስ ያሳደሩብኝ ተፅኖ ከፍተኛ ነው።ለማስታወስ የክል ያን ጊዜ 2007 ዓ.ም ሀምሌ 05 ቀን ወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ከተመረኩ በኋለ የኢትዬጵያ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ባህርዳር ቅ/ጽ/ቤት ኮንትራት ቅጥር አውጥቶ ከጓደኞቼ ጋር ተወያይቼ አንዳንዶቹ ኮንትራት ቅጥር አንሞክርም ሲሉ አንዱ ጓደኛየ ግን ቅጥር ስ... | gojjam | 0G2FAS | female | |
የጤና ስርአት ላይ መለወጥ ብችል ቅድሚያ የምለወጠው የጤና ኬላወችን ለህብረተሰቡ አማካኝ በሆነ ቦታ በቅርብ እርቀት ላይ እየገነቡ በቃሬዛ መሄድ ቀርቶ ማህበረሰቡ በቀላሉ ወደ ህክምና ቦታወች ሳይገላቱ ደሰ ብሏቸው በመሄድ ጤናቸውን እንዲጠብቁ ማድረግ ።በደንብ እየተሰራ ያለ የጤና ስርአት ወላዶችን በእንክብካቤ የማዋለድ ስርአት ይበል የሚያሰኝ ሲሆን በአንጻሩ ደግሞ በደንብ ያልተሰራበት ስለ ካንሰር በሽታ አስከፊነት ለምሳሌ ህብረተሰቡ ሰለ ካንሰር በሽታ ጥንቃቄ ማድረግ እዳለበት የግንዛቤ እጥረት አለ ሀኪም ... | gojjam | 0G2FAS | female | |
በማህበረሰቤ ውስጥ በዓል ሲከበር፣ የሚታየው ድባብ ሰዎች በዓልን ለማክበር የሚያደርጉት የተለመዱ ተግባራት ቤተሰቦች እና ጓደኞች በማግኘት የማህበረሰብ ጸሎቶች ይደረጋል ልዩ ቀሚሶችን ወይም ልብሶችን ምሳሌ፦ እንደ ነጭ ልብስ በመልበስ ቤተሰቦች በአንድ ሞሰብ በመቀመጥ በጋራ ይበላሉ በግጥሞች እና በድምፅ ዘፈኖች እዘፈኑ መጨፈር
እርስ በርስ ሽልማት መለዋወጥ ይካሄዳል።ይህ ሁሉ ህዝባዊ ደስታን እና የጋራ አክብሮትን የሚፈጥር ሲሆን፣ እያንዳንዱ በዓል የራሱ ባህላዊ ጥልቀት እና ማህበራዊ ሚና አለው። | gojjam | 0G2FAS | female | |
በአካባቢያችን በየሰው ቤት የሚወጣን ቆሻሻ በሳምንት አንዴ ከአንድ ላይ ተሰብስቦ ከተጠራቀመ በኃላ ቆሻሻን በሚሰበሰብ የተደራጀ ማህበር በየአካባቢው እየዞረ በመኪና ተሰብስቦ ወደ ቆሻሻ መጣያ ወደ ተዘጀው ቦታ ይወሰዳል። አንዳንድ ሰዎች ኑሮአቸውን ለማሻሻል ሲሉ ከቆሻሻው ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ብረቶችን፣ማዳበሪያዎችን፣ ፕላስቲኮችን(ጎማዎችን) ለይቶ በመሰብሰብ ለተለያዩ ጥቅም ሪሳይክል እንዲውሉ በኪሎ ለነጋዴ በማስረከብ ኑሮአቸውን ይደጉማሉ አንዳንዶች ደግሞ የወደቁ ሀይላንድ ጎማዎችን (ፕላስቲኮችን) በመ... | gojjam | 0G2FAS | female | |
በእኔ ህይወት በአብዛኛው ግዜ ውሳኔወችን ስወስን በምክንያታዊነት ነው። ምክንያቱም ነገ ለሚገትመኝ ችግር መፍትሄ ለማበጀት አሁን ላይ የምወስነው ውሳኔ ትልቅ ሚና ይጫወታል። ውሳኔውቼን በስሜት ብወስን ለዛን ሰአት ጥሩ ውሳኔ መስሎ ለሌላ ጊዜ እኔን ትልቅ ችግር ውስጥ ሊከተኝ ይችላል በዚህ ምክንያት ውሳኔወቼን ስወስን በስሜታዊነት ሳይሆን በምክንያታዊነት ነው የምወስነው። | gojjam | 0G2FAS | female | |
ባዓላትን ከቤተሰብ ጋር የማከብርዉ ሰዉ እንደቤቱ እንጅ እንደጎረቤቱ አይደለም በሚለዉ አባባል ፣በባህላችን መሠረት እንደአቅማችን ቤትያፈራዉን በማዘጋጁት እናከብራለን።እንጀራበመጋገር፣ዳቦበመድፍት፣ወይም በመጋገር፣ጠላበመዘ
ጠላበመበጥበጥ፣ቡናበማፍላትእናከብራለን።ለምሳሌ ፍሲካ ቢሆን ደሮ በማረድ፣ሥጋበማስገባት እነዚህ ካደአግን በኀላ ከእኛ ያነሱትን ወይም ድሆችን በማብላት፣ጎረቤት በመጥራት፣ዘመድአዝማድበመጥራት በጋራ በመሆን በደስታ፣በፍቅር ሁነን በማሠባሠብ እናከብራለን ።በመጨረሻም በእየድሜ ደረጃቸው እንመ... | gojjam | 0G2FAS | female | |
ያን ያህል ብዙ ቦታ ለመጎብኘት እድሉን አላገኘሁም ። ነገርግን ጣና ሀይቅ በጣም ሚያምረዉ ያየሁት ቦታ ነዉ። ጣና በምሄድበት ጊዜ መንፈሴ ታድሶ ነዉ ምመለሰው ። ጣና ከመዝናኛነት በላይ መንፈሳዊ ጉዞ ለማድረግ በጣም ተመራጭ ነዉ ምክንያቱም በውስጡ የደሴት ገዳማት ይገኙበታል ። በተለይም ደግሞ አሁን ላይ የተደረጉ አከባቢውን የማስዋብ ስራዎች በጣም ውብ እና ለመዝናናት አመቺ አድርገውታል ። | gojjam | 0G2FAS | female | |
እንግዶችን በምንቀበልበት ጊዜ እንደ ቆሎ፣ ቡና፣ ጠላ ወይም ጭማቂ ያሉ ምግቦችን እና መጠጦችን እናቀርባለን፡፡ ምክንያቱም ከፍትፍቱ ፊቱ እንደሚባለው ምግብ ማቅረብ የተለመደ የእንግዳ ተቀባይነት ባህል ነው፡፡
እንግዳ ተቀባይነትን ለማሳየት አስፈላጊ ናቸው ተብለው የሚታሰቡ ልዩ ምግቦች በባህል ይለያያሉ፡፡ ነገር ግን ብዙ ጊዜ በእኛ አካባቢ እንግዳ ተቀባይነትን ለማሳየት ከሚቀርቡ ተወዳጅ ምግቦች እና መጠጦች ውስጥ ዶሮ ወጥ በእንጀራ፣ ቡና፣ ጠላ ወ.ዘ.ተ. የመሳሰሉት ምግቦች እና መጠጦች የቀርባሉ፡፡ | gojjam | 0G2FAS | female | |
አብዛኛው ማህበረሰብ የሞባይል ስልክ ይጠቀማል:: ይሄም በመሆኑ ሰዎች መረጃዎችን ከተለያዩ አማራጭኦች ያገኛሉ :: ለምሳሌ ከሞባይል ስልክ ላይ ራድዬ አለ ከሱ ብዙ መረጃዎችን ይሰማሉ:: ከሱ በተጨማሪ ፌስቡክ እና ቴሌቪዥን ላይም የተለያዩ መረጃዎች አሉ:: የዜና አማራጭ ከቲቪ እና ራድዬ ያገኛሉ:: ምርጫቸውም አባይ ቲቪ፣ ኢቲቪ እና አሻም ቲቪ ሲሆን እነዚህንም የመረጡበት ምክንያት ከሚያስተላልፉት ወቅታዊ እና እውነተኛ መረጃ አንፃር ነው :: | gojjam | 0G2FAS | female | |
**የእንጨት ስራ እና የሸክላ ስራ፦ *የእንጨት ስራዎች * የቤት እቃዎች: በእጅ የተቀረጹ ጠረጴዛዎች፣ ወንበሮች እና አልጋዎች ፣የልብስ መያዣ ሳጥን ፣ለከብት ውሀ ማጠጫ የሚሆን ከበታ ፣ሙገጫ(የቡና እና የበርበሬ መውገጫ) ጀበና (የቡና ማፍያ ማሰሮ)፣ የውሃ ማጠራቀሚያ ጋን ፣ ማድጋ እና ምንቸት የሸክላ ድስቶች ለምግብ ማብሰያ የሚያገለግሉ የተለመዱ የሸክላ ውጤቶች ናቸው። *ሌላው የእጅ ስራ ጥጥ መፍተል *ጥልፍ መጥለፍ *ለጌጣጌጥ የሚሆኑ ኪሮስ መስራት ከዚህ በላይ ያሉ ሁሉም ባደኩበት አካባቢ የሚሰሩ የእ... | gojjam | 0G2FAS | female | |
ጤንነቴን እና ደህንነቴን ለመጠበቅ፣ በርካታ ጠቃሚ ልማዶችን እከተላለሁ። የተመጣጠነ ምግብ እበላለሁ፣ በቀን ከሁለት ሌትር ያላነሰ ውሃ እጠጣለሁ፣ እና እራሴን ለመጠበቅ አዘውትሬ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እሰራለሁ። እንዲሁም በቂ እንቅልፍ እተኛለሁ እና እንደ አልኮል ወይም ትምባሆ ካሉ ጎጂ ሱሶች እቆጠባለሁ። በተጨማሪም የእራሴን እና የአካባቢዬን ንፅህና እጠብቃለሁ። የህመም ስሜት ሲሰማኝ የጤና ባለሙያወችን አማክራለሁ ። እራሴን እና ሌሎችን ለመጠበቅ አልባሌ ቦታወች ላይ አልገኝም። እነዚህም ድርጊ... | gojjam | 0G2FAS | female | |
ሃይማኖታዊ በዓላት ለምሳሌ፣ በትንሣኤ ወቅት ሰዎች አብረው ይጾማሉ፣ ከሚበሉት ምግብ ያጋራሉ፣ ይህም የማህበረሰብ ቅንጅት ዋጋ ያለው ያደርገዋል። የጋራ የማህበረሰብ በዓላት ለምሳሌ፣ እንቁጣጣሽ (የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት) በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚከበር ሲሆን፣ ሰዎች አብረው ይበላሉ፣ ይዘፍናሉ እና ተስፋ ያደርጋሉ። በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ያሉ የተለያዩ ቡድኖች በአንድ ዓላማ ይሰባሰባሉ ለምሳሌ በችግር ወቅት ሰዉ ሲታመም ወይም ሲሞት ማህበረሰቡ እንደ አንድ ቤተሰብ በጋራ ይሰራል። ትውልድ ለትውልድ እሴቶች... | gojjam | 0G2FAS | female | |
ዜጎች የትራንስፖርት ችግራቸውን የመቅረፍ እድል ያገኛሉ ፤ከዚህም በተጨማሪ የትራንስፖርት ወጪያቸውን በእጅጉ ይቀንሳሉ ፤ ከአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች የመላመድ እና ቴክኖሎጂውን የራስ የማድረግ ምቹ ሁኔታን ይፈጥርላቸዋል እንዲሁም የሚጠቀሙት የትራንስፖርት መንገድ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ በመሆናቸው በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ቀስ በቀስ ወደ ሀገር የመግባት እድላቸው ስለሚቀንስ ዜጎች የአየር ብክለትን ከመቆጣጠር አንፃር የድርሻቸውን ይወጣሉ።ዜጎች ደግም ሁል ጊዜ ወጪ ቆጣቢና አካባቢን የማይበክል የትራንስፖርት አማ... | gojjam | 0G2FAS | female | |
አደንዛዥ እፆችን መጠቀም በአካላዊ ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያመጣል። ለምሳሌ የልብና የአካል አካላት ችግር፣ የጉበትና የኩላሊት አደጋ፣ እና የእንቅልፍ ችግር ይፈጥራል። በአይምሮአዊ ጤና ላይ ደግሞ እንደ እርምጃ መቋረጥ፣ ማስታወስ ችግር፣ የሐሜት እና የጭንቀት ህመም ይያዛል።
በጎጃም አካባቢ በባህል የተለመዱ ነገሮች ውስጥ ጉዳት ያላቸው እፆች ጫት፣ ሲጋራ እና አልኮል መጠጦች ናቸው። ጫት ብዙ ጊዜ የአይምሮአዊ ጉዳት ያመጣል፣ እንቅልፍ ይከለክላል እና የስራ ብቃትን ያሳንሳል። አልኮል ግን የጉበት አደጋ፣... | gojjam | 0G2FAS | female | |
ቤተሰቦቻቸው በቅድሚያ ያበሳጫቸውን ነገር በመለየት ለምንድነው ብሎ በመጠየቅ ምክር መስጠት እና ለቀጣይ እንዲስተካከል በምሳሌ አስደግፈው መመካከር እና በጋራ በመወያየት ቁጣን የሚያስነሳ ጉዳዮችን በድጋሜ እንዳይፈጠር ማድረግ ነው። | gojjam | 0G2FAS | female | |
የኛ አካባቢ ማህበረሰብ ባህላዊ ውዝዋዜ ስልት የጎጃሙ እንቅጥቅጥ ወይም ዝናቡ የተሰኘው ሁሉም ዘፈን ውስጥ የገቡት ሰዎች በጋራ የሚጨፍሩበት የድለቃ ስልትን ነው።ይህ የድለቃ ወይም የጭፈራ ስልት ሁሉም ዘፈን ውስጥ የገቡት ሰዎች ክብ በመስራት ፊት ለፊታቸው ከሚደልቀው ጓደኛቸው ጋር እየተያዩ ያዘኝ ምታ በመበባል ሁላቸው አንድ ጊዜ የሚጨፍሩት መንገድ ነው።ይህ የጭፈራ አይነት "ተው ምታ" በመበባል መሬቱን አቧራው እስከሚቦል ድረስ እየዘለሉ በእግራቸውም ይመቱታል። | gojjam | 0G2FAS | female | |
ብዙ ወጣቶች ከገጠር ወደ ከተማ የሚሙጡት በተለይ ለትምህርት እና ለስራ የተሻለ ነገር ይፈልጋሉ። ብዙውን ጊዜ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታቸውን ለማሻሻል እና ከተለምዷዊ እና ባህላዊ አስተሳሰቦች ነፃ ለመውጣት በተስፋ ይነሳሳሉ። ለምሳሌ አንድ ወጣት ከቀየው ወጥቶ ዩኒቨርሲቲ ለመማር ወይም የፋብሪካ ወይም የጉልበት ሥራ ለማግኘት ከገጠር ወደ ከተማ ይመጣል። ይህንን የህይወት ለውጥ ብዙውን ጊዜ የሚመጣው እራሱን ለመቀየር ፣ በገንዘብ እራስን ለመቻል እና ለዘመናዊ የአኗኗር ዘይቤ ባለው ፍላጎት ነው። | gojjam | 0G2FAS | female | |
በእኛ አካባቢ ለነዋሪወች የሚሆኑ መገልገያወች እንደ ክሊኒኮች፣ ትምህርት ቤቶች ቀበሌወች እና የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በዚህ ሰአት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። በአሁን ጊዜ አሪፍ የሚባል ሁኔታ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ። አሁን ላይ ክልላችን ባጋጠመው የፀጥታ ችግር ምክንያት ስራ መቆራረጥ እና አለመኖር ቢኖርም አሪፍ የሚባል መስተንግዶ የሚሰጡ ናቸው። ያለው የፀጥታ ችግር የሚስተካከል ከሆነ ከዚህ በፊት እንደነበረው ጥሩ መስተንግዶ ይሰጣሉ ብየ አስባለሁ። | gojjam | 0G2FAS | female | |
ተግባራትን በማስቀደም እና ወደ ትናንሽ፣ ማስተዳደር በሚቻል ደረጃዎች በመከፋፈል ወደ ሁለገብ ስራ እቀርባለሁ። ለእያንዳንዱ ተግባር የተወሰኑ ሰዓቶችን ለመስጠት ጊዜን ማቀድን አስቀድማለሁ። መርሃ ግብር መፍጠር፣ለስራ፣ ለቤተሰብ ጊዜ እና ለራስ እንክብካቤ ተግባራት የተወሰኑ ጊዜዎችን በመመድብ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴን መንደፍ የተሻለ ሚዛን ለማግኘት ይረዳል። የቤተሰብን መርሃ ግብር፣ የስራ ግዴታዎችዎን እና የግል ግቦችን ግምት ውስጥ ማስገባት እና ለእራስ የበለጠ የሚሰራ እቅድ ማውጣት። ግቦችን በትክክል... | gojjam | 0G2FAS | female | |
የእኔ ቤተሰቦች ወይም የአካባቢያችን ማህበረሰብ ብዙ አይነት የእንግዳ መቀበያ ልምዶች ወይም ባህሎች አሉ፡፡ለምሳሌ፦የመጀመሪያው አንድ እንግዳ" ደህና ዋላችሁ"ብሎ ደጅ ላይ ሲቆም አግዚአብሄር ይመስገን ተብሎ ዝቅ ብሎ ጉልበቱን ስሞ የያዘውን ዱላ ወይም ብትር ተቀብሎ ወደ ቤት ማስገባት ነው።ከዚያ በመቀጠል ቤት ያፈራውን እንደሁኔታው ቡና ይፈላል፣የቡና ቁርስ ይቀርባል፣ የተለያዩ ባህላዊ መጠጦች ጠላ፣አረቂ፣ከተማ አካባቢ ከሆነ ደግሞ ቢራ እና ቀዝቃዛ መጠጦች ይቀርባል። | gojjam | 0G2FAS | female | |
እኔ በስፋት ሲማሩ ማየት የምፈልጋቸው ርዕሰ ጉዳዮች አገር በቀል እውቀቶች ላይ እና የቤተሰብ አመሰራረት ስነ-ስርዓቱ ላይ ነው።
-አገር በቀል እውቀት ማለት እጅግ በጣም አስፈላጊ ሲሆን። ለምሳሌ የራስ ችግርን በራስ ለመፍታት፣ ባህልን አስጠብቆ ለማስቀጠል፣በራስ አገር ሀብት ለመጠቀም እና ለመመራመር፣ የመሳሠሉት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በስፋት ሲማሩ ማየት እፈልጋለሁ።
-የቤተሠብ አመሠራርት ስነ-ስርዐቱ፦ ይህ ማለት ቤተሠብ ሲመሰረት በልጆች ፈቃድ ላይ ብቻ መመስረቱ ከቁጥጥር እና ከተጠያቂነት ወጭ የሆነ ትውልድ... | gojjam | 0G2FAS | female | |
1. አረግ እሬሳ ወይም ዕጸ ሳቤቅ ፣
2.ግራዋ፣
3.ኮሶ ፣
4.አረቂ እና ቡና እና ሌሎችም አሁን አላስታውሳቸው ያልኩት ነገሮች ለመድሀኒትነት ይውላሉ።
ዕጸ ሳቤቅ የምትባለው ዛፍ በመጠጋት የምታድግና የምትመዘዝ ዐረግ ስትሆን ምች ለመታውና ለታመመ ሰው ትሆናለች ከባሕር ዛፍ ቅጠል ጋር ቀላቅሎ በመቀቀል ውሀው መልኩ ሲቀይርና ሲበስል መታጠን ፣ ወይም መቀባት። ግራዋ ደግሞ ፊኛ ውጋት ላመመው ሰው በጥብጦ ማጠጣት።
ኮሶ ላለበት ሰው ደግሞ ኮሱ እንዲጠጣ ይደረጋል።አረቂና ቡና ደግሞ ለሰዎችም ሆነ ለእንስሳት ቁ... | gojjam | 0G2FAS | female | |
እርዳታ ወይም ድጋፍ በብዙ አይነት መልኩ ሊገለፅ ይችላል ይህ ሲባል እኔ በምኖርበት አካባቢ ያለው ማህበረሰብ በኑሮ ደረጃ ሁሉም ባይባልም ዝቅተኛ ነዋሪ ህብረተሰብ ይበዛበታል በገንዘብ ብቻም ሳይሆን በአስተሳሰብ(አመለካከት)ደካማ ነው ስለዚህ እኔ በአካባቢየ እረዳት(ድጋፍ)ለሚፈልግ ሰው በገንዘብ ባልደግፍም በሀሳብ፣ታላላቅ ሰዎችን በመታዘዝ፣አቅመደካሞችን በመንከባከብ(ልብሳቸውን ማጠብ፣ቤታቸውን መጠገን)ሴቶች እህቶቻችን ጥቃት ሲደርስባቸው ወደሚፈለገው ቦታ መውሰድ አስፈላጊውን እርዳታ(መፍትሄ) እንዲያገኙ ማድ... | gojjam | 0G2FAS | female | |
እንደኔ አሁን ላይ ብዙም ሀላፊነት የለኝም ከቤተሰብ ጋር ስለምኖር የስራም ይሁን ሌሎች ሀላፊነቶች ላይ እብዛም አደሉም።ያው አንዳንዴ ሲገጥመኝ ሁሌ ባልተገብረውም ፕሮግራም አወጣለሁኝ በዚህ በዚህ ሰአት ጊዜ ይሔንን ብሰራ በዚህ በዚህ ሰአት ደግሞ ለእንደዚህ እያልኩ አቅዳለሁኝ ። ለምሳሌ ጥዋት ጥዋት ስፖርት መስራት፣ቤተክርስቲያን መሔድ ከዛ መልስ ቤት ማስተካከል ማፅዳት ቁርስ መስራት... እንደዛ እንደዛ እያልኩ የቀን ውሎየን በፕሮግራም እመራለሁኝ ።እና ደግሞ መቅረት የማይቻልበት ጉዳይ ላይ ቅድሚያ አስፈ... | gojjam | 0G2FAS | female | |
አዎ!
ስለ እድር ዓላማ እና አስፈላጊነት ሲጠየቅ፡-
እድር በተለያዩ ማህበረሰቦች ውስጥ የተለያዩ ሚናዎች ሊኖሩት ይችላል። አንዳንድ ማህበረሰቦች ውስጥ እድር ለሚከተሉት ዓላማዎች ሊያገለግል ይችላል፡-
1. የጋራ ውሳኔ ለማሳለጥ - ውሳኔዎችን በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለማሳለጥ
2. ልምድ እና እውቀት ለማጋራት - አባላት የተለያዩ ችሎታዎችን እና እውቀትን ለማጋራት
3. ማህበረሰብ ግንኙነት ለማጠናከር - በአባላት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር
ሆኖም ግን፣ እድር በማህበረሰብ ውስጥ አስፈላጊ እንደሆ... | gojjam | 0G2FAS | female | |
ማህበራዊ ሚዲያ በግልጽ ግጭትን ለመፍታት እና ሰዎችን አንድ ላይ ለማምጣት በተለያዩ ሁኔታዎች አዎንታዊ ተጽዕኖ አሳይቷል። ለምሳሌ፣በሰሜኑ ጦርነት ጊዜ ማህበራዊ ሚዲያ የህዝብን ድምፅ ለማሰማት፣ ለተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ሰዎችን ለማንቃት እና ለድጋፍ እንቅስቃሴዎች ለማሰባሰብ በጣም ጠቃሚ ሆኗል። እንዲሁም በግልጽነት ያቀረበ መረጃ በቡድኖች መካከል የግጭት መፍትሄን በአዎንታዊ መንገድ ለማግኘት አግዟል።
ለህዝብ አንድነትና ማህበረሰባዊ ጥቅም የሚያስገኙ መረጃዎችን ሲጠቀሙ ማህበራዊ ሚዲያ በግጭት መፍትሄ ውስ... | gojjam | 0G2FAS | female | |
አንድ የአካል ጉዳት ያለበት ሠው ከቤተሠቦቹ እሱ በአካል ጉዳቱ ከማንም አንደማያንስ እና አንድ ጤነኛ ሰው ሊሠራ የሚችለውን ስራ በብቃት መስራት እንደሚችል ማሳመን አለባቸው። እና ለትምህርት የሚያፈልጉትን እና ተጨማሪ ረጂ መሳሪያ እና የሚሄድበትን መንገድ ማመቻቸት አለባቸው። ትምህርትቤቱ ደግሞ ለአካል ጉዳተኛ የሚሆን ክፍል እና ልዩ ድጋፍ ማድረግ አለባቸው። በአካላቸው ምክንያት መገለል እነሰዳይደርስባቸው መጠበቅ አለበት። | gojjam | 0G2FAS | female | |
አዎን፣ በዕድሜ የገፉ ሰዎች በብዙ ማህበራዊ እና ባህላዊ አካባቢዎች ስሜታቸዉን በተለያዩ መንገዶች ያሳያሉ ።ይህ የሚታየዉ በባህል ፣ በልምድ ፣ በአስተሳሰብ እና በእድሜ የሚመጣ ልዩነቶች ምክንያት ነዉ ። የሚታዩት ልዩነቶች በእድሜ የገፉት በጉዳይ ላይ ቀጥተኛ መሆን የተለመደ ነው፣ ነገር ግን ክርክር አይወዱም።።ክፉ ሁኔታ እሚመጣ ቢሆንም በብዛት ይቀርፉአቸዋል፣ እርምጃ ለመውሰድ በቀስታ ይወስናሉ። በልምዳቸው ልክ ምክር ለመስጠት ይሞክራሉ። በተቃራኒ ወጣቶች በእጅጉ ቀጥተኛ ይሆናሉ፣ አንዳንድ ጊዜ ስለሰው ... | gojjam | 0G2FAS | female | |
ከቁርስ በተጨማሪ ፍራፍሬ እመገባለሁ ለምሳሌ፦ ሙዝ ፣ ብርቱካን እና የአቦካዶ ጁስ እመገባለሁ። ለምሳ ብዙ ጊዜ እምመገበዉ ያዉ ዋነኛዉ ምርጫየ እንጀራ ነዉ ሽሮ ፣ ቀይወጥ ፣ ምስር ፣ድንች ነዉ ። እራት ደሞ እማይከብድ ምግብ መብላትን እመርጣለሁ ምክንያቱም በልቼ ስለማልቀሳቀስ ይከብደኛል በአብዛኛዉ እምበላዉ ሽሮ ፣ አትክልት እመገባለሁ ። እነዚን ምግቦች እምመገበት ቦታ አብዛኛዉን ጊዜ ቤት ዉስጥ እራሴ አብስየ ነዉ ያዉ አንዳንዴ ስራ ሲበዛብኝ እና ሲረፍድብኝ ካፌ ወይም ሬስቶራንት ላይ አዝዠ ልመገብ እች... | gojjam | 0G2FAS | female | |
የእንጨት ስራ
ማለት እንጨቶችን በመጠቀም የተለያዩ ጌጦችን በማውጣት ውብ እና ማራኪ አድርጎ ሰዎች እንዲጠቀሙባቸው የማድረግ የሙያ አይነት ነው። ሰዎችም ከአልጋ ሶፋ ወንበር ሳጥን እና የተለያዩ እቃዋችን ማስቀመጫ አድርገው ያጠቀሙባቸዋል።
የሸክላ ስራ
ማለት ጭቃን በመጠቀም ለተለያዩ መገልገያዎች የሚሰሩበት ጥበብ ነው። እነሱም በእየለት ተግባራችን የምንጠቀምባቸው እቃዎችን እና ጌጦችን ይጨምራል።ለምሳሌ ጀበና ድስት የአበባ ማስቀመጫ ወዘተ ናቸው | gojjam | 0G2FAS | female | |
ስኳር፣ሶላር መብራት፣የድንች መፋቂያ፣የውሀ ፓምፕ እና ሌሎችም አሁን ያላስታወስኋቸው ቁሳቁሶች በእኛ ገበያ ለማግኘት ከባድ ነው።ፓምፕ እንዲያውም በግብርና የተሰጠ ሰው ካልተዋዋስን በሰተቀር ገበያ ላይ ብዙ ጊዜ አይገኝም።ሌሎች ነገሮች አንኳ ከሌላ ከተማ ስለማይታጡ ከዚያ እየሄድን እንገዛለን።ለምሳሌ ስኳር እኛ ገበያ ብዙም የለ በቀበሌ ካልሆነ እና ከደብረ ማርቆስ ወይም ከ አዲስ አበባ የሚመጣ ሰው ካለ በዛ አድርጎ እንዲያመጣልን እንነግረዋለን። እኛ ቤተሰብ እነደዚያ ነው ያችን እየቆጠቡ መጠቀም ነው። | gojjam | 0G2FAS | female | |
የአካባቢ ብክለት ለጀርሞችና ባክቴሪያዎች መራቢያ ስለሚሆን ሰዎች በቀላሉ በበሽታ እንዲጠቁ ያደርጋቸዋል ከዚህ በተጨማሪ የተፈጥሮን የአየር ሁኔታ ስለሚቀይር ሰዎች የመተንፈሻ አካላቸው ጤነኛ እንዳይሆን እንዲሁም የሳንባ በሽተኛ ያርጋቸዋል።
የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስ፦ቆሻሻን በተለያዩ መንገድ ማስወገድ ይኖርባቸዋል።ለምሳሌ የፈሳሽ ቆሻሻ ማፋሰሻ ጉድጓድ በመቆፈር በዚያ ላይ ማፋሰስ፣ ደረቅ ቆሻሻን በአንድ ላይ በማጠራቀም ማቃጠል የመሳሰሉት ናቸው | gojjam | 0G2FAS | female | |
የሚለው ዋና ጥያቄ ሲሆን ፣ተጨማሪም የተረቶችን አና በልይነት ዘዴዎችን እንደ ምሣሌ ይጥቅማል።
በመጀመሪያ ፣የተጠቃው
የተጠቃሚዉ የልጅች አሰተዳደር ወይም አስተማሪ እንደሆኑ አስባለሁን ።ልጅ እንደ ዉሀ። ነው ፤የሚገኘውን ቅረጽ ይይዛል "የሚለው ተረት ያስታወሱት "በልጆች ዙርያ ያለው አካባቢ ፣በቤት ዉስጥ ያሉ ስረዓቶች አና የእርሰዋ ባሀሪ በእነሱ ስነምግባር ለይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ ያሳድራሉ ።በትዕግስት፣ዉስጥት አና ፍቅር በማሳየት ሀቀኛ አና ስርአት ሰው ያላቸው ሰዋች እንደሆሂ ያበረታታችዉ።
| gojjam | 0G2FAS | female | |
ማህበረሰቡ ቆሻሻን የሚያስወግድበት መንገድ ቆሻሻውን በተደባለቀ መንገድ ሲሆን ይህም ቆሻሻውን በመሰብሰብ ላይ ለተሰማሩ ግለሰቦች በጣም አስቸጋሪ ነው። በዚህ የተደባለቀ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ስልት ብዙዎች በሚለዩበት ወቅት የተለያየ የጤና እክል ያጋጥማቸዋል። ነገር ግን ማህበረሰቡ ቆሻሻውን ለይቶ ቢያስቀምጥ ለመልሶ መጠቀምም ሆነ የሚሰበሰብበትን ግለሰቦች ማገዝ ይቻል ነበር።
ቆሻሻን መልሶ በመጠቀም እንደ ባዮ ጋዝ፣ የተፈጥሮ የአፈር ለምነት ማስጠበቂያ ማዳበሪያ እና ለሌሎች ጥቅም ማህበረሰቡ መጠቀም ይችል ነበ... | gojjam | 0G2FAS | female | |
በጌሳምንቱ ቢያንስ 100ብር እወጣለሁ እሄ ለባጃጅ ነው ለሽኳንታ ደግሞ አንዳንድ ጊዜ ዘመድ ለመጠየቅ 500 ብር አወጣለሁ። እሄን ለመቀነስ ገበያ ለመሄድ በእሬ እሄዳለሁ። | gojjam | RI43PH | female | |
አዎ አዲስ ሰው ወደ ቤት ሲመጣ ''ቤት እንቦሳ '' በማለት ይገባል ።የቤቱ ባለቤትም ''እንቦሳ እሰር '' ብሎ ይመልሳል | gojjam | RI43PH | female | |
የሃገር ሽማግሌዎችን ማክበር፣ እና ለህግ ተገዥ መሆን ። | gojjam | RI43PH | female |
Leyu Amharic - Gojjam Dialect Speech Corpus
Dataset Description
This dataset is a curated parallel speech corpus consisting of audio recordings paired with corresponding text transcripts, focused on the Gojjam dialect of the Amharic language. It is designed to support speech technology research across multiple tasks, including Automatic Speech Recognition (ASR) and Text-to-Speech (TTS). The corpus captures dialect-specific phonetic variations, accent patterns, and prosodic characteristics that are essential for building dialect-aware and robust speech systems.
All recordings were collected in real-world environments using mobile devices, introducing natural acoustic variability that improves model generalization. Each audio–text pair underwent manual review to ensure transcript accuracy and audio clarity. By emphasizing demographic diversity and regional authenticity, the dataset contributes to the advancement of inclusive and representative speech technologies for low-resource African languages.
Dataset Summary
| Metadata Field | Value |
|---|---|
| Language | Amharic (am-ET) |
| Dialect | Gojjam |
| Audio Format | .wav |
| Total Hours | 81.59 Hours |
| Recording Environment | Mobile / Crowdsourced (Verified) |
Key Statistics
- Total Duration: 81.59 Hours
- Speaker Count: 82 Speakers (Male: 45, Female: 37)
- Data Quality: Mobile-recorded and manually verified for transcript alignment.
Data Collection & Quality Assurance
- Recorded by contributors using mobile devices in real-world environments.
- Manually reviewed to ensure transcript alignment and audio clarity.
Data Fields
Each sample contains:
text(string): transcriptaudio(Audio): waveform/audio filedialect(string):gojjamspeaker_id(string): anonymized speaker identifiergender(string):male/female/unknown
gheero Blogs
- Leyu: Crowdsourcing Datasets for Ethiopian Languages
- Dialects & Socioeconomics: Shaping Inclusive Language Models
- Progress of Natural Language Processing (NLP) for Ethiopian Languages – Part One
- Progress of Natural Language Processing (NLP) for Ethiopian Languages – Part Two
- Data Collection with Purpose: The Leyu Approach
- Downloads last month
- 349